ተዛማጅ ወገኖችን መለየት፣ አምስቱ ዘዴዎች በተሠሩ ስሌቶች፣ ንጽጽሮችና የIQR ክልል፣ Management fee፣ ብድርና ኪራይ፣ የLocal file አጻጻፍና የ45 ቀን የባለሥልጣን ጥያቄ — 180 ገጽ የአማርኛ መመሪያ፣ 17 ሉህ Excel ሲስተም ከ2,451 ቀመሮች ጋርና 26 ዝግጁ ቅጾች፣ ውሎችና ደብዳቤዎች።

በቪዲዮው ውስጥ የሚያዩት ከእውነተኛዎቹ ፋይሎች የተወሰዱ ገጾችን ነው።
ፋብሪካዎ ለእህት ኩባንያዎ አከፋፋይ ይሸጣል? የውጭ ባለአክሲዮንዎ የአስተዳደር ክፍያ ያስከፍላል ወይም ብድር ሰጥቶዎታል? ቢሮዎ የቤተሰብ አባል ንብረት ነው? የገንዘብ ሚኒስቴር የትራንስፈር ፕራይሲንግ መመሪያ ቁ. 981/2024 ዓመታዊ ሽያጭዎ ከ500,000 ብር በላይ ከሆነ ከተዛማጅ ወገኖች ጋር ያደረጉት እያንዳንዱ ግብይት — የአገር ውስጥም ዓለም አቀፍም — ነፃ ወገኖች በሚስማሙበት ዋጋ ("Arm's length") መሆኑን የሚያሳይ ሰነድ እንዲኖርዎ ያዝዛል። ሰነዱ በግብር ተመላሽ ቀን ዝግጁ መሆን አለበት፤ ባለሥልጣኑ በጽሑፍ ሲጠይቅ በ45 ቀናት ውስጥ ይቀርባል። ሰነድ ከሌለ ቅጣቱ እስከ 20% የዘመኑ ግብር ሊደርስ ይችላል — ዋጋዎ ትክክል ቢሆንም እንኳ፤ ዋጋዎ ከነፃ ገበያ ክልል ውጪ ከሆነ ደግሞ ባለሥልጣኑ ገቢዎን ወደ መካከለኛው አስተካክሎ ተጨማሪ ግብር ይጠይቃል።
እነዚህ ምስሎች ከExcel ሲስተሙ የተወሰዱ ናቸው። ቁጥሮቹ ምሳሌ ናቸው። ለማስፋት ምስሉን ይጫኑ።









ከመመሪያው እና ከቅጾቹ የተወሰዱ ገጾች። ለማስፋት ይጫኑ።
ወደ Ye-Buna የምርቱ ገጽ ይወስድዎታል።
በTelebirr፣ በCBE Birr ወይም በM-Pesa።
ክፍያው እንደተጠናቀቀ የማውረጃ ሊንክ ይደርስዎታል።
ዓመታዊ ሽያጭዎ ከ500,000 ብር በላይ ከሆነና ከተዛማጅ ወገን (25% ወይም ከዚያ በላይ የሚይዝዎ ወይም የሚይዙት፣ የባለቤቶች ዘመዶች፣ የጋራ ባለቤት ያላቸው ድርጅቶች) ጋር ዕቃ፣ አገልግሎት፣ ብድር፣ ኪራይ ወይም ሮያሊቲ ከተገበያዩ — አዎ፣ ይመለከትዎታል። መመሪያ 981/2024 የአገር ውስጥ የቁጥጥር ግብይቶችንም ይሸፍናል። መመሪያው ምዕራፍ 5 የ5 ደቂቃ ራስን መፈተሻ፣ ምዕራፍ 13 ደግሞ የቤተሰብ ቡድኖችን ልዩ ስጋት ያብራራል።
ሰነዱ በግብር ተመላሽ ማቅረቢያ ቀን ዝግጁ መሆን አለበት፤ ባለሥልጣኑ በጽሑፍ ሲጠይቅ በ45 ቀናት ውስጥ ይቀርባል። ካልቀረበ ቅጣቱ እስከ 20% የዘመኑ ግብር ሊሆን ይችላል (ግብር ከሌለ ምንጮች የተለያየ ቋሚ መጠን ይጠቅሳሉ — መመሪያው ምዕራፍ 2 እና 15 ልዩነቱን ያሳያሉ)። ምዕራፍ 66 የ45 ቀኑን የሥራ ዕቅድ ቀን በቀን ይሰጣል።
ብዙ ጊዜ የሚያስፈልግዎ መረጃ በእጅዎ ነው፦ ተመሳሳዩን ዕቃ ከነፃ ወገን የሚገዙበት ወይም የሚሸጡበት ዋጋ፣ ከአቅራቢዎች የተሰበሰቡ የዋጋ ማቅረቢያዎች፣ የባንክ ወለድ ተመኖች፣ የደላላ የኪራይ ግምትና የታተሙ የሂሳብ መግለጫዎች። መመሪያው ምዕራፍ 39–44 ምንጮቹን ከጠንካራ ወደ ደካማ ይዘረዝራል፤ የ8 ደረጃ ፍለጋውንና የውጭ ንጽጽሮችን አጠቃቀም ያሳያል። በፋይሉ ውስጥ ያሉት ንጽጽሮች ምሳሌ ናቸው።
በ«ቅንብሮች» የኩባንያዎን ስም፣ የግብር ዓመትና የተመላሽ ቀን ያስገባሉ፤ በ«የፋይናንስ መረጃ» የትርፍና ኪሳራ ቁጥሮችን፣ በ«ተዛማጅ ወገኖች» ግንኙነት ያላቸውን፣ በ«የቁጥጥር ግብይቶች» (200 ረድፎች) ግብይቶቹን ይመዘግባሉ። ከዚያ ለእያንዳንዱ ግብይት ተገቢውን ማስያ ከፍተው ንጽጽሮችን ያስገባሉ — ማስተካከያ፣ ግብር፣ ሙሉነትና ዳሽቦርዱ በራሳቸው ይሰላሉ። ቢጫ ሴሎች ላይ ብቻ ይጻፉ፤ ፋይሉ ማክሮ የለውም።
የለውም። ፋይሉ .xlsx ነው — ሁሉም ስሌቶች በተለመዱ የExcel ቀመሮች ይሰራሉ።
Microsoft Excel 2016፣ 2019፣ 2021 ወይም Microsoft 365 ይመከራል። መረጃ ለማስገባት ኮምፒውተር የተሻለ ነው።
በስልክዎ በExcel መተግበሪያ ገጾቹን ማየትና ቁጥር መቀየር ይችላሉ፤ መመሪያውና ቅጾቹም በስልክ ይከፈታሉ። ለሙሉ ሥራ ግን ኮምፒውተር ይመከራል።
ፋይሉ በምሳሌ መረጃ ተሞልቶ ይመጣል። የምሳሌውን ቁጥሮች በራስዎ መረጃ ይተካሉ — ቀመሮቹ ቀሪውን ያሰላሉ። የWord ቅጾቹን በድርጅትዎ ስምና መረጃ ያስተካክላሉ።
ክፍያዎ በYe-Buna እንደተጠናቀቀ የማውረጃ ሊንክ ይደርስዎታል። ZIP ፋይሉን አውርደው ይከፍቱታል።
የክፍያውን ማረጋገጫ (SMS ወይም ደረሰኝ) ይዘው ያግኙን — ፋይሉን እንልክልዎታለን።
የትራንስፈር ፕራይሲንግ ሰነድ ኪት — በእህት ኩባንያዎች መካከል ለሚደረግ ግብይት — መመሪያ 981/2024 — 3,499 ብር፣ አንድ ጊዜ ክፍያ።
አሁን ይግዙ →