ከዝርያና ከእርሻ መጠን ምርጫ፣ ከዶሮ ቤት፣ ከመኖና ከክትባት እስከ ባንኩ የሚፈልገው የቢዝነስ ፕላን፣ የ5 ዓመት የፋይናንስ መግለጫዎች፣ DSCR፣ የትርፍ ነጥብ፣ NPV/IRR እና ትብነት — 105 ገጽ የአማርኛ መመሪያ፣ 20 ሉህ Excel ሞዴል ከ16,650 ቀመሮች ጋርና 28 ዝግጁ የWord ቅጾችና አብነቶች።

በቪዲዮው ውስጥ የሚያዩት ከእውነተኛዎቹ ፋይሎች የተወሰዱ ገጾችን ነው።
ብዙ የዶሮ ፕሮጀክቶች ብድር የሚከለከሉት በዶሮው ሳይሆን በፕላኑ ነው። ባንኩ የሚቀርብለት ሰነድ ብዙ ጊዜ ቁጥሮቹ የማይገናኙበት፣ መኖ ከሥራ ማስኬጃ ወጪው ከግማሽ በላይ መሆኑ ያልታሰበበት፣ ጣዮቹ እስኪጥሉ ያሉት ወራት የገንዘብ ጫና ያልተሰላበትና የብድሩ የመክፈያ አቅም (DSCR) ያልታየበት ነው። ይህ ጥቅል የዶሮውን ቴክኒካል ጎን ከባንኩ ጎን ጋር አስተሳስሮ ፕላንዎን በቁጥር እንዲያቀርቡ ያግዝዎታል።
እነዚህ ምስሎች ከExcel ሲስተሙ የተወሰዱ ናቸው። ቁጥሮቹ ምሳሌ ናቸው። ለማስፋት ምስሉን ይጫኑ።









ከመመሪያው እና ከቅጾቹ የተወሰዱ ገጾች። ለማስፋት ይጫኑ።
ወደ Ye-Buna የምርቱ ገጽ ይወስድዎታል።
በTelebirr፣ በCBE Birr ወይም በM-Pesa።
ክፍያው እንደተጠናቀቀ የማውረጃ ሊንክ ይደርስዎታል።
በ«ቅንብሮች» ሉህ ከ6 ሁኔታዎች (A–F፦ 500፣ 1,000፣ 2,000 ወይም 5,000 ጣይ፣ ወይም ሥጋ ዶሮ ብቻ) አንዱን ይመርጣሉ፤ የጫጩት፣ የመኖ፣ የእንቁላልና የሥጋ ዶሮ ዋጋዎችን፣ የብድሩን ወለድ፣ ጊዜና እፎይታ ያስገባሉ። ቤት፣ ሠራተኛ፣ ኢንቨስትመንት፣ 260 ሳምንት ምርትና ሁሉም መግለጫዎች በራሳቸው ይቀየራሉ። ቢጫ ሴሎች ላይ ብቻ ይጽፋሉ።
አያረጋግጥም። ጥቅሉ ባንኮች የሚጠይቋቸውን ክፍሎችና ስሌቶች (የፕሮጀክት ወጪ፣ መዋጮ፣ የፋይናንስ መግለጫዎች፣ DSCR፣ ትብነት) በሥርዓት እንዲያዘጋጁ ያግዛል፤ ውሳኔው የባንኩ ነው። ፋይሉ ማክሮ የለውም — በExcel 2010+ እና በLibreOffice ይሠራል።
የለውም። ፋይሉ .xlsx ነው — ሁሉም ስሌቶች በተለመዱ የExcel ቀመሮች ይሰራሉ።
Microsoft Excel 2016፣ 2019፣ 2021 ወይም Microsoft 365 ይመከራል። መረጃ ለማስገባት ኮምፒውተር የተሻለ ነው።
በስልክዎ በExcel መተግበሪያ ገጾቹን ማየትና ቁጥር መቀየር ይችላሉ፤ መመሪያውና ቅጾቹም በስልክ ይከፈታሉ። ለሙሉ ሥራ ግን ኮምፒውተር ይመከራል።
ፋይሉ በምሳሌ መረጃ ተሞልቶ ይመጣል። የምሳሌውን ቁጥሮች በራስዎ መረጃ ይተካሉ — ቀመሮቹ ቀሪውን ያሰላሉ። የWord ቅጾቹን በድርጅትዎ ስምና መረጃ ያስተካክላሉ።
ክፍያዎ በYe-Buna እንደተጠናቀቀ የማውረጃ ሊንክ ይደርስዎታል። ZIP ፋይሉን አውርደው ይከፍቱታል።
የክፍያውን ማረጋገጫ (SMS ወይም ደረሰኝ) ይዘው ያግኙን — ፋይሉን እንልክልዎታለን።
የዶሮ እርባታ ቢዝነስ ፕላን ለባንክ ብድር — የእንቁላል ጣይና የሥጋ ዶሮ፣ ከነ 5 ዓመት የፋይናንስ ትንበያ — 1,999 ብር፣ አንድ ጊዜ ክፍያ።
አሁን ይግዙ →