ከማጣሪያ፣ ToR፣ የተጽዕኖ ግምገማና ሕዝባዊ ምክክር እስከ ESMP ትግበራ፣ ክትትል፣ ቅሬታ፣ ዓመታዊ እድሳትና ኦዲት — 181 ገጽ የአማርኛ መመሪያ፣ 19 ሉህ Excel ሲስተም ከ9,308 ቀመሮች ጋርና 28 ዝግጁ ቅጾችና አብነቶች።

በቪዲዮው ውስጥ የሚያዩት ከእውነተኛዎቹ ፋይሎች የተወሰዱ ገጾችን ነው።
በ2025 የወጣው የአካባቢና ማኅበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ አዋጅ ቁ. 1371/2025 ለ23 ዓመታት ሲሠራበት የነበረውን አዋጅ 299/2002 ተክቷል። በሕግ ማጠቃለያዎች መሠረት ማረጋገጫው ቋሚ መሆኑ ቀርቶ በየዓመቱ ይታደሳል፣ ESMP በየ3 ዓመቱ ተሻሽሎ ይቀርባል፣ ባለሥልጣኑ ቢያንስ በ2 ዓመት ኦዲት ያደርጋል፣ ግምገማው ከ15 ወደ 45 የሥራ ቀን ተራዝሟል፤ የንግድና የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሰጪዎችም ማረጋገጫውን ይጠይቃሉ። ያለ ማረጋገጫ ሥራ የመጀመር ቅጣት ከ50,000–100,000 ብር ወደ 500,000–10,000,000 ብር ማደጉን የሕግ ኩባንያ ማጠቃለያዎች ያሳያሉ (ከዋናው አዋጅ ያረጋግጡ)። ብድር ከጠየቁ ደግሞ ባንኮችና DFIዎች በIFC Performance Standards ወይም በዓለም ባንክ ESF መሠረት ESIA፣ ESMP፣ የቅሬታ ሥርዓትና ወቅታዊ ሪፖርት ይጠይቃሉ። ስለዚህ ESIA አሁን የአንድ ጊዜ ወረቀት ሳይሆን የዓመታዊ ሥራ አካል ነው። ይህ ኪት ሙሉውን ሂደት በቀላል አማርኛና በአንድ የምሳሌ ፋብሪካ ቁጥሮች ደረጃ በደረጃ ያስተምራል፣ መዝገቦቹን በExcel ያደራጃል፣ የሚቀርቡትን ሰነዶችም ዝግጁ ያደርጋል።
እነዚህ ምስሎች ከExcel ሲስተሙ የተወሰዱ ናቸው። ቁጥሮቹ ምሳሌ ናቸው። ለማስፋት ምስሉን ይጫኑ።









ከመመሪያው እና ከቅጾቹ የተወሰዱ ገጾች። ለማስፋት ይጫኑ።
ወደ Ye-Buna የምርቱ ገጽ ይወስድዎታል።
በTelebirr፣ በCBE Birr ወይም በM-Pesa።
ክፍያው እንደተጠናቀቀ የማውረጃ ሊንክ ይደርስዎታል።
የነጋሪት ጋዜጣው መረጃ (31ኛ ዓመት ቁ. 37፣ 11 April 2025)፣ የዓለም ባንክ ሰነዶችና የዓለም አቀፍ የሕግ ቋቶች «1371/2025» ይላሉ። አንዳንድ የሕግ ማጠቃለያዎችና ዘገባዎች «1317/2025» ብለው ጽፈውታል። መመሪያው ምዕራፍ 6 ይህን ያብራራል፤ በይፋ ደብዳቤ ላይ ቁጥሩን ከነጋሪት ጋዜጣው ቅጂ አረጋግጠው ይጥቀሱ።
አያስቀርም። በአዋጁ መሠረት የESIA ጥናት የሚዘጋጀው በባለሥልጣኑ ፈቃድ ባላቸው ባለሙያዎች ነው (መመሪያ 1005/2024)። ኪቱ ግን ፕሮጀክትዎ ምን እንደሚያስፈልገው እንዲያውቁ፣ ግልጽ ToR እንዲያዘጋጁ፣ የአማካሪውን ሪፖርት እንዲገመግሙና ከጸደቀ በኋላ ESMPን፣ ክትትሉንና ዓመታዊ እድሳቱን ራስዎ እንዲቆጣጠሩ ያስችልዎታል።
ሊመለከትዎ ይችላል። በሕግ ማጠቃለያዎች መሠረት ESIA ያልተሠራላቸው ነባር ፕሮጀክቶች በአንድ ዓመት ውስጥ ESMP እንዲያቀርቡ የሽግግር ድንጋጌ አለ። መመሪያው ምዕራፍ 11 ሁኔታውንና የምሳሌ ፋብሪካው ነባር ክፍል እንዴት እንዳስተናገደው ያሳያል፤ ዝርዝሩን ከባለሥልጣኑ ወይም ከክልልዎ ተቋም ያረጋግጡ።
በ«ቅንብሮች» የፕሮጀክቱን መረጃ፣ የሪፖርት ቀን፣ ኢንቨስትመንትና ገደቦች ያስገባሉ፤ ከዚያ ማጣሪያውን፣ የተጽዕኖ ማትሪክሱንና የጉልህነት ምዘናውን ይሞላሉ፣ ESMP እርምጃዎችንና የክትትል ውጤቶችን ይመዘግባሉ። በጀቱ፣ ወርሃዊ ማጠቃለያው፣ ማረጋገጫውና ዳሽቦርዱ በራሳቸው ይሰላሉ። ቢጫ ሴሎች ላይ ብቻ ይጻፉ። Macro የለውም።
የለውም። ፋይሉ .xlsx ነው — ሁሉም ስሌቶች በተለመዱ የExcel ቀመሮች ይሰራሉ።
Microsoft Excel 2016፣ 2019፣ 2021 ወይም Microsoft 365 ይመከራል። መረጃ ለማስገባት ኮምፒውተር የተሻለ ነው።
በስልክዎ በExcel መተግበሪያ ገጾቹን ማየትና ቁጥር መቀየር ይችላሉ፤ መመሪያውና ቅጾቹም በስልክ ይከፈታሉ። ለሙሉ ሥራ ግን ኮምፒውተር ይመከራል።
ፋይሉ በምሳሌ መረጃ ተሞልቶ ይመጣል። የምሳሌውን ቁጥሮች በራስዎ መረጃ ይተካሉ — ቀመሮቹ ቀሪውን ያሰላሉ። የWord ቅጾቹን በድርጅትዎ ስምና መረጃ ያስተካክላሉ።
ክፍያዎ በYe-Buna እንደተጠናቀቀ የማውረጃ ሊንክ ይደርስዎታል። ZIP ፋይሉን አውርደው ይከፍቱታል።
የክፍያውን ማረጋገጫ (SMS ወይም ደረሰኝ) ይዘው ያግኙን — ፋይሉን እንልክልዎታለን።
የአካባቢና ማኅበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ ESIA/ESMP ኪት — አዋጅ 1371/2025 — 3,999 ብር፣ አንድ ጊዜ ክፍያ።
አሁን ይግዙ →